
የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ባፕቲስት ቤተክርስትያን በዳላስ ቴክሳስ የእግዚአብሔርን አምላክነት የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነትና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በዳላስ ቴክሳስና በተለያዪ ቦታዎች በማወጅ የእግዚአብሔር መንግሥትን እያሰፋፋች ያለች፣ ያለመኑትን እንዲያምኑ፣ ያመኑት ደግሞ በእግዚአብሔር ጸጋ እንዲያድጉና እንዲጸኑ በትጋት እይሰራች ያለች ቤተክርስቲያን ናት።
ይህንን ሃላፊነት በትጋት እንድንወጣ ባለፉት ዓመታት የረዳንን እግዚአብሔርን እያመሰገንን ከፊታችን ላለው የሥራ ዘመን በበለጠ ትጋት የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋት እየሰራች ትገኛለች።
ይህንን ከክርስቶስ የተቀበልነውን ሃላፊነት የምንተገብርበት ዋና መመሪያችን የሕያው እግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
በዚህ ቃል ላይ ትመርኩዘን የቤተክርስቲያኒቱ የእምነት መግለጫ በዝርዝር ተቀምጧል፤ በይበልጥ ለመረዳት ከታች ያለውን "የእምነት መግለጫ" መጎብኘት ይችላሉ
እግዚአብሔር ይባርኮት!
የኢትዮጵያውያን ወንጌላዊት ባፕቲስት ቤተክርስቲያን
በዳላስ ቴክሳስ የእምነት መግለጫ
EEBC Dallas Texas
Statement of Faith
መያያዝ
Connect /Join
ወደ የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ቤተክርስትያን በዳላስ ቴክሳስ ድህረ ገጽ በመምጣት ስለጎበኙን እናመሰግናለን። መኖሪያዎ በዳላስ ቴክሳስ አካባቢ ከሆነ 3001 Saturn Rd, Garland, TX 75041 በሚገኘው አጥቢያ በመገኘት አብረን እግዚአብሔርን እንድናመልክ እና የክርስቶስን ጸጋ አብረን እንድንከፋፈል በጌታ ፍቅር እንጋብዝዎታለን። በተጨማሪም የቤተክርስትያናችን ቤተሰብ ለመሆን ከወሰኑ ወይንም ጥያቄ ካለዎት ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን ሊያገኙን ይችላሉ።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝ አድርገው ከተቀበሉና የውሃ ጥምቀት ለመውሰድ የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን ማስፈንጠሪያ (Link ) በመጫን ሊያገኙን ይችላሉ
የቤተክርስትያናችን አባል ከሆኑ፣ በቤት ለቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ኅብረት ሕይወትዎን በእግዚአበሔር ቃል እንዲያሳድጉና ከሌሎች ጋር ኅብረት እንዲያደርጉ ቤተክርስትያን በጽኑ ታበረታታለች። በቤት ለቤት ኅብረት ለመያያዝ ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን ሊያገኙን ይችላሉ።
የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ቤተክርስትያን በዳላስ ቴክሳስ አባሎቿ በሕይወታቸው እንዲያድጉና እንዲጸኑ ካዘጋጀቻቸው መንገዶች አንዱ ጠንካራ ቤተሰብን በመገንባት ጠንካራ ትውልድን ለእግዚአብሔር መንግስትና ለአገር ጠቃሚ ዜጋን ማዘጋጀት ቀዳሚ ሥራዋ እንደሆነ አምና ይህንን ኅብረት አዘጋጅታ ምእመኖቿን እያስታጠቀች ትገኛለች።
በዚህ ማዘጋጀት ሂደት ውስጥ የእርሶ ቤተሰብ በዚህ ኅብረት መያዝ ትልቁን ሚና ስለሚጫወት እርሶና ቤተሰቦን የዚህ በረከት ተካፋይ እንዲሆኑ በጌታ ፍቅር እንጋብዝዎታለን።
በተጨማሪም ጥያቄ ካለዎት ወይም የዚህ ኅብረት ተጥቃሚ ለመሆን ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን ሊያገኙን ይችላሉ።
የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ቤተክርስትያን በዳላስ ቴክሳስ ባለብዙ የአገልግሎት ዘርፍ ስትሆን ይህንን በተቀላጠፈ መንገድ ለመስራት የተዋቀሩ የአገልግሎት ክፍሎች አሏት በእነዚህ ክፍሎች በአንዱ ለማገልገል ወይም ጥያቄ ካሎትና ለማግኘት ከፈለጉ ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን ሊያገኙን ይችላሉ።